ባህር ዳር ከተማ አጥቂ አስፈረመ

አጥቂው ፋሲል አስማማው በሁለት ዓመት ውል የጣና ሞገደኞቹን ተቀላቅሏል፡፡

ከኢንስትራክተር አብረሃም መብራቱ የአሰልጣኝነት መንበሩን የተረከቡት ደግአረገ ይግዛው ከሹመታቸው በፊት በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች ክለቡን መቀላቀል የቻሉ ሲሆን አሰልጣኙ በመንበራቸው ከተሾሙ በኋላ ግን ሁለተኛ ፈራሚያቸውን ረዘም ያሉ ዓመታትን በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ያሳለፈውን አጥቂው ፋሲል አስማማውን በይፋ አስፈርመዋል፡፡

ተጫዋቹ ወደ ባህር ዳር ያቀናው ለሁለት ዓመታት በሚዘልቅ ውል ነው።

ያጋሩ