በቀድሞ የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች የተነሳው ቅሬታ ያሬድ ባየ እንደማይመለከተው ገለፀ

ያሬድ ባየ ከፋሲል የለቀቁ ተጫዋቾች ባነሱት ቅሬታ ውስጥ አለመኖሩን ሲገልፅ ግብ ጠባቂው ደግሞ ሀሳባቸውን ተጋርቷል።

በትናትናው ዕለት ስድስት የቀድሞ የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች ‘ቃል የተገባልን የሽልማት ገንዘብ አልተሰጠንም’ በማለት በወከሉት አንድ ተጫዋች አማካኝነት ቅሬታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ልከው ዘገባ ሰርተን እንደነበር አይዘነጋም።

በዚህ ዘገባ ውስጥ ስድስቱ ተጫዋቾች መካከል ስሙ ተጠቅሶ የነበረው ያሬድ ባዬ ቅሬታ የሌለው መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን አሳውቋል። በሌላ በኩል ግን ከፋሲል ከነማ ጋር ላለፉትን አራት አመታት ቆይታ የነበረው ግብ ጠባቂው ቴዎድሮስ ጌትነት እንደሌሎቹ አምስት ተጫዋቾች ‘ለእኔም የተገባው ቃል አልተፈፀመልኝ’ በማለት ቅሬታ እንዳለው ነግሮናል።

የክለቡ የበላይ አካል በዚህ ጉዳይ ነገ ውይይት አድርጎ አቅጣጫ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙ ታውቋል።