የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድሮች የሚጀመሩበት ጊዜ ታውቋል

የ2015 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ውድድሮች የሚጀመሩባቸውን ጊዜያት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከሰዓታት በፊት የ2015 የኢትዮጵያ ወንዶች ከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ የውድድር ኅዳር 3 እንደሚጀምር ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ውድድሮች የሚጀመርባቸውን ጊዜያት በድረ-ገፁ አቅርቧል።

በዚህም የውድድር ዳይሬክቶሬት ባሳወቀው መሰረት የሁለቱም ሊጎች የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ጥቅምት 22/2015 የሚከናወን ሲሆን በተመሳሳይ ሁለቱም ውድድር ህዳር 10/2015 እንደሚጀምር ተጠቁሟል። ከዚህ ቀደም ከጳጉሜ 1/2014 – ህዳር 15/2015 ሆኖ የወጣው የዝውውር ጊዜ ላይ ማሻሻያ ተደርጎ ደግሞ ክለቦች እስከ ጥቅምት 25 ድረስ ብቻ ዝውውር እንዲፈፅሙም ውሳኔ መተላለፉን አመላክቷል።