አዳማ ከተማ የተከላካይ አማካይ አስፈረመ

ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ከሰሞኑ የተለያየው የተከላካይ አማካዩ ዳንኤል ደምሱ በይፋ አዳማ ከተማን ተቀላቅሏል፡፡

በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ እየተመራ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከፋሲል ከነማ ጋር በማድረግ የዘንድሮው የውድድር ዘመን ጅማሬ የሚያደርገው አዳማ ከተማ ከቀናት በፊት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በጋራ ስምምነት የተለያየውን የተከላካይ አማካዩ ዳንኤል ደምሱን በይፋ አስፈርሟል፡፡

በወልድያ ከተማ ፣ ኢትዮጵየ ቡና ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና በበርካታ ክለቦች ውስጥም ጭምር ተጫውቶ ያሳለፈው ዳንኤል ለቀጣዩ አንድ ዓመት ለአዳማ ግልጋሎት ለመስጠት አምርቷል፡፡

ያጋሩ