ፈረሰኞቹ የአጥቂያቸውን ውል አራዝመዋል

ከደቂቃ በፊት አማኑኤል ገብረሚካኤልን በቡድናቸው ያቆዩት ፈረሰኞቹ የሌላኛውን አጥቂያቸውን ውል ማራዘማቸውም ታውቋል።

ለ2015 የውድድር ዘመን ዛሬ ወደ ባህር ዳር ያቀኑት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የወሳኝ አጥቂያቸውን አማኑኤል ገብረሚካኤልን ውል ካካዘሙ በኋላ አሁን ደግሞ የአዲስ ግደይን ውል ማራዘማቸውን አውቀናል።

በሲዳማ ቡና ለአራት ዓመታት ቆይታ አድርጎ በ2013 የፈረሰኞቹ ቤት የተቀላቀለው አዲስ ግደይ ከጉዳት ጋር እየታገለ ክለቡን ሲያገለግል መቆየቱ ሲታወቅ ለተጨማሪ አንድ አመት በቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያቆየውን ውል ማራዘሙም ታውቋል።