ወላይታ ድቻ ስያሜው ላይ ማስተካከያ አድርጓል

ከዚህ ቀደም ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረው ክለብ ከዚህ በኋላ “ድቻ ስፖርት ክለብ” በሚል እንደሚጠራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በቅርቡ እንዳስታወቀው የብሔር እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስያሜዎችን የሚጠቀሙ ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ባወጣው መመሪያ መሰረት ወላይታ ድቻ ቀዳሚው ማስተካከያ ያደረገው ክለብ ሆኗል።

በዚህም መሠረት ከዚህ ቀደም “ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ” በሚል ይጠቀምበት የነበረውን መጠርያ ወደ “ድቻ ስፖርት ክለብ” ስለመለወጡ ክለቡ ለፌደሬሽኑ አሳውቋል።

በቀጣይ ሌሎች ክለቦችም ማስተካከያ ያደርጋሉ ተብሎም እንደሚጠበቅ ፌደሬሽኑ አያይዞም ገልጿል።

ያጋሩ