ኢትዮጵያዊው ዳኛ ተጠባቂውን የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ይመራል

የሱዳኑ አልሂላል ከ ታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ ጋር በኦምዱርማን የሚያደርጉትን የቻምፒየንስ ሊግ የመልስ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያዊው አልቢትር በመሀል ዳኝነት ይመራዋለ፡፡

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ካለንበት ሳምንት ጀምሮ መደረግ ይጀምራሉ፡፡ በዚህ አህጉራዊ የክለቦች ውድድር ላይ ተካፋይ የሆነው እና ቅዱስ ጊዮርጊስን በመጀመሪያ ማጣሪያው በመርታት ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፈው የሱዳኑ አልሂላን ከታንዛኒያው ሀያል ክለብ ያንግ አፍሪካ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያዊው አልቢትር በመሀል ዳኝነት እንደሚመራው ታውቋል፡፡

መስከረም 28 ዳሬሰላም ላይ ያንግ አፍሪካ በሜዳው ከአልሂላል ጋር ከተጫወተ በኋላ ጥቅምት 6 ሱዳን ኦምዱርማን ላይ የሚደረገውን የመልስ መርሐግብር ኢትዮጵያዊው ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በመሀል ዳኝነት እንዲመሩ በካፍ ስለመመረጣቸው ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡