ዳሽን ቢራ 1-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ
6′ የተሻ ግዛው | 59′ አዳነ ግርማ 61′ ምንተስኖት አዳነ
ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ
ተጠናቀቀ!!!
ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታውን 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ አንድ ጨዋታ እየቀረው 1ኛውን ዙር በመሪነት ማጠናቀቁንም አረጋግጧል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
89′ ሸሪፍ ዲን በኦዶንካራ እና መሃሪ አለመግባባት ያገኘውን ጥሩ የግብ ማስቆጠር እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
86′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
በሃይሉ አሰፋ ወጥቶ አይዛክ ኢዜንዴ ገብቷል፡፡
83′ ሸሪፍ ዲን ከርቀት የሞከረው ኳስ አግዳሚውን ታኮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
81′ ዳዋ ሁቴሳ ገብቶ ራምኬል ሎክ ወጥቷል፡፡
80′ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ጉዳት እያስተናገዱ ጨዋታውም በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ይገኛል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ዳሽን ቢራ
78′ መስፍን ኪዳኔ ገብቶ የተሻ ግዛው ወጥቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
74′ ምንያህል ተሾመ ወጥቶ ዘካርያስ ቱጂ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ዳሽን ቢራ
67′ መሀመድ ሸሪፍ ዲን ገብቶ ኤዶም ሆሶውሮቪ ገብቷል፡፡
66′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረውታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ዳሽን ቢራ
64′ ደረጄ መንግስቴ ገብቶ ምንያህል ይመር ወጥቷል፡፡
61′ ጎልልል!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
ምንተስኖት ከመሃሪ የተሻገረለትን ኳስ መሬት ለመሬት በመምታት ቅዱስ ጊዮርጊስን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል፡፡
59′ ጎልልል!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
አዳነ ግርማ ከማዕዘን የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡
55′ ጨዋታው የመጀመርያው አጋማሽ መልክን ይዞ ቀጥሏል፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በዳሽን ቢራ 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
45+1′ መሃሪ መና ከግራ መስመር የሞከረው ኳስ የግቡ አግዳሚ ገጭቶበታል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ቢጫ ካርድ
42′ ኤዶም ሆሶሮውቪ በደጉ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
30′ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኳስ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት በመሄድ የተሻለ ቢሆንም የዳሽንን ጥብቅ መከላከል ሰብሮ መግባት አልቻሉም፡፡ ዳሽን ቢራ ደግሞ በፈጣን መልሶ ማጥቃት አደጋ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡ በርካታ የማዕዘን ምቶችንም ማግኘት ችለዋል
21′ በግምት ከ35 ሜትር ርቀት የተገኘውን የቅጣት ምት በሃይሉ መትቶ የዳሽን ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውበታል፡፡
20′ ጊዮርጊሶች ጎል ከተቆጠረባቸው በኃላ ጫና ቢፈጥሩም ይህ ነው የሚባል ሙከራ አላደረጉም፡፡ ዳሽን በአንፃሩ በመልሶ ማጥቃት ወደ ጊዮርጊስ ግብ ለመቅረብ እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡
6′ ጎልልል!!! ዳሽን ቢራ!!!
ዳሽን ቢራ በየተሻ ግዛው ግብ ቀዳሚ ሆኗል፡፡ በመልሶ ማጥቃት የተገኘውን ኳስ የተሻ ከርቀት በመምታት በኦዶንካራ መረብ ላይ በግሩም ሁኔታ አሳርፎታል፡፡
2′ አዳነ በግምት ከሰላሳ ሜትር ርቀት የግብ ጠባቂውን መውጣት ተመልክቶ የሞከረውን ኳስ ቴዎድሮስ እንደምንም አውጥቶበታል፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
09:02 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ በመግባት ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ፡፡
08:52 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
08:32 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች እንዲሁም ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች ወደ ሜዳ ገብተው በማማሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የዳሽን ቢራ አሰላለፍ (4-3-3)
ቴዎድሮስ ጌትነት
ዮናስ ግርማይ – አለማየሁ ተሰማ – ያሬድ ባየህ – አምሳሉ ጥላሁን
ሳሙኤል አለባቸው – አስራት መገርሳ – ምንያህል ይመር
ኤርሚያስ ሃይሉ – ኤዶም ሆሶውሮቪ – የተሻ ግዛው
ተጠባባቂዎች
ቢንያም ሀብታሙ ፣ ሱሌይማን አህመድ ፣ ኦስማን ካማራ ፣ መስፍን ኪዳኔ ፣ ደረጄ መንግስቴ ፣ መሀመድ ሸሪፍ ዲን ፣ ማይክ ሰርጂ
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ (4-3-3)
ሮበርት ኦዶንካራ
አንዳርጋቸው ይላቅ – ደጉ ደበበ – አስቻለው ታመነ – መሀሪ መና
ምንያህል ተሾመ – ተስፋዬ አለባቸው – ምንተስኖት አዳነ
ራምኬል ሎክ – አዳነ ግርማ – በኃይሉ አሰፋ
ተጠባባቂዎች
ፍሬው ጌታሁን ፣ አበባው ቡታቆ ፣ ዘካርያስ ቱጂ ፣ ዳዋ ሁቴሳ ፣ አቡበከር ሳኒ ፣ አይዛክ ኢዜንዴ ፣ አለማየሁ ሙለታ