ከፍተኛ ሊግ | ጋሞ ጨንቻ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

የከፍተኛ ሊጉ ተካፋዩ ጋሞ ጨንቻ አዲስ አሰልጣኝ አግኝቷል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ እየተመራ በምድብ ሀ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው የደቡቡ ክለብ ጋሞ ጨንቻ ለዘንድሮው የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል፡፡

ግዛቸው ጌታቸው የክለቡ አዲሱ አሰልጣኝ ሆኗል፡፡ በቀኝ መስመር ተከላካይነት በሀላባ ከተማ እና ወላይታ ድቻ እግር ኳስን ተጫውቶ ያሳለፈው ግዛቸው እግር ኳስን ካቆመ በኋላ የወላይታ ድቻን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድንን በዋና እንዲሁም የዋናው ቡድን በረዳት አሰልጣኝ ከዚህ ቀደም ያገለገለ ሲሆን ለያዘው የውድድር ዘመን ደግሞ የከፍተኛ ሊጉን ክለብ ጋሞ ጨንቻን በአሰልጣኝነት ለማገልገል የአንድ ዓመት ውል መፈራረሙ ታውቋል።