የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ተራዘመ

በሱዳን አስተናጋጅነት የሚደረገው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ቀድሞ ከወጣለት ቀን በአንድ ሳምንት ተገፍቶ ይጀመራል፡፡

በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሴካፋ አስተናጋጅነት የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች የ2022 ውድድር በሱዳን አስተናጋጅነት ይከናወናል፡፡ በሰባት የዞኑ ሀገራት መካከል በሚደረገው ውድድር ላይ አስተናጋጇን ሀገር ሱዳንን ጨምሮ ዩጋንዳ ፣ ጅቡቲ ፣ ብሩንዲ ፣ ታንዛኒያ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ በማሳተፍ አስቀድሞ ከጥቅምት 12 ጀምሮ በካርቱም ከተማ ላይ እንደሚጀመር ቀደም ብሎ ሴካፋ አሳውቆ የነበረ ቢሆንም ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሠረት ውድድሩ በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ጥቅምት 18 እንዲጀመር መወሰኑን ማረጋገጥ ችለናል፡፡

በአሰልጣኝ ዕድሉ ደረጀ መሪነት በውድድሩ ተካፋይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅቱን እየከወነ የሚገኝ ሲሆን ከብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰዓታት በኋላ ወደ እናንተ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል፡፡

ያጋሩ