ቅዱስ ጊዮርጊስ ስድስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው የአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊው ቅዱስ ጊዮርጊስ የስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል፡፡

በ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ማራኪ እግርኳስን ካስመለከቱን ቡድኖች መካከል የሚጠቀሰው የቅዱስ ጊዮርጊስ የዕንስቶች ቡድን ለዘንድሮው የ2015 የውድድር ዘመን ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት በአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ መሪነት ክለቡን ያጠናክሩልኛል ያላቸውን ስድስት ተጫዋቾች ዝውውር ፈፅሟል፡፡

በአርባምንጭ ከተማ እና ያለፈውን ዓመት ደግሞ በአዲስ አበባ ቆይታ የነበራት ግብ ጠባቂዋን ድንቡሽ አባን ጨምሮ ቤዛዊት ደምሴ ከንፋስ ስልክ ተከላካይ ፣ ፀግሸት አራጌ ከአራዳ ክፍለከተማ ተከላካይ ፣ ሀናን ረዲ ከሱሉልታ ተከላካይ ፣ መሠረት ገዛኸኝ ከአራዳ አማካይ እና ቤተልሄም ጌታቸው ከአራዳ አማካይ ቅዱስ ጊዮርጊስን መቀላቀናቸውን ክለቡ አስታውቋል።

ያጋሩ