ቡናማዎቹ በዛሬው ጨዋታ በዋና አሠልጣኛቸው አይመሩም

አሠልጣኝ ተመስገን ዳና በዛሬው ጨዋታ ቡድናቸውን እንደማይመሩ ታውቋል።

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ 7 ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ተጠባቂውን ጨዋታ ያከናውናሉ። ሲዳማ ቡናዎች ከሰሞኑን አሠልጣኝ ሥዩም ከበደን ቢሾሙም የወረቀት ሥራዎች ባለመገባደዳቸው ሲዳማዎች በምክትል አሠልጣኛቸው በጨዋታው ሲመሩ ቡናማዎቹም ዛሬ በምክትሎቻቸው እንደሚመሩ ታውቋል።

በቅርቡ ወንድማቸውን አጥተው የነበሩት አሠልጣኝ ተመስገን ዳና አሁን ደግሞ ወላጅ አባታቸው ህልፈታቸው በመሰማቱ ለሀዘን ወደ ሀዋሳ እየተጓዙ በመሆኑ ቡድኑን እንደማይመሩ ታውቋል።

ይህንን ተከትሎም ተጠባቂው ጨዋታ በምክትል አሠልጣኞች የሚመራ ይሆናል።

ያጋሩ