ከፍተኛ ሊግ | ነገሌ አርሲ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል

በከፍተኛ ሊጉ የ2014 የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው ነገሌ አርሲ ዋና አሰልጣኝ ሾሟል፡፡

በአምናው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በምድብ ሀ ስር ተደልድሎ አስደናቂ የውድድር ዘመን አሳልፎ በመጨረሻም በ34 ነጥቦች ምድቡን በሦስተኛ ደረጃ ፈፅሞ የነበረው ነገሌ አርሲ አሰልጣኝ ራህመቶ መሐመድን ለሀላባ ከተማ አሳልፎ በመስጠቱ በምትኩም በረዳት አሰልጣኝነት ያሳለፈው እና ለአምስት ዓመታት ክለቡን ያገለገለውን በሽር አብደላን በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል፡፡

አሰልጣኝ በሽር በእግርኳስ ተጫዋችነቱ በነገሌ አርሲ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ ሚዛን ቴፒ ፣ መቂ ከተማ እና ደደቢት በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን በጉዳት ከእግር ኳስ ከተገለለ በኋላ ያለፉትን አምስት ዓመታት በነገሌ አርሲ የረዳት አሰልጣኝነት ሚና ላይ ከሰራ በኋላ አሁን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ያጋሩ