አዲስ አበባ ከተማ የአሰልጣኝ ሽግሽግ ሲያደርግ በርከታ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተወዳዳሪ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ የአሰልጣኝ ሽግሽግ በማድረግ አስራ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ ዝግጅት ጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ከሚወዳደሩ ክለቦች መካከል የመዲናይቱ ክለብ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ ይጠቀሳል፡፡ ያለፈው የውድድር ዓመት በሀያ አምስት ነጥቦች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስድስተኛ ላይ ተቀምጦ የፈፀመው ቡድኑ ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ባለፈው ዓመት ረዳት አሰልጣኝ የነበረው አብዱራህማን ዑስማንን በዋና አሰልጣኝነት ፣ ዋና አሰልጣኝ የነበረችው የሺሃረግ ለገሰን በረዳት አሰልጣኝነት ቦታ ላይ ሽግሽግ በማድረግ አስራ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝግጅታቸውን ጀምረዋል፡፡

ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚዎች

ግብ ጠባቂ: ባንቺአየው ደመላሽ (ከድሬዳዋ ከተማ) ፣ አይናለም ሽታ (ከቅዱስ ጊዮርጊስ)

ተከላካዮች: ገነት ፈርዳ (ድሬዳዋ) ፣ ሰብለ ቶጋ (አዳማ) ፣ ሳምራዊት ኃይሉ (አዳማ) ፣ ትዕግስት አስረስ (አዳማ) እና መሠረት ማሞ (ሀምበሪቾ)

አማካዮች: ኪፊያ አብዱራህማን (ሀዋሳ) ፣ የካቲት መንግስቱ (ድሬዳዋ) ፣ ማህሌት ታደሰ (አዳማ) ፣ መዲና ጀማል (መከላከያ) እና ሰናይት መኩሪያ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

አጥቂዎች: ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ) ፣ አስራት አለሙ (ድሬዳዋ) ፣ ቤተልሄም መንተሎ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፍሬህይወት ተስፋዬ (ንፋስ ስልክ) ፣ ምህረት ቱንጆ (ጉለሌ) ፣ ሰላማዊት ተስፋዬ (ንፋስ ስልክ) እና አብነት ጎበና (ቂርቆስ)

ክለቡ ከአዳዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ የአምስት ነባሮችን ውልም ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡