ወላይታ ድቻ ከጋናዊው አጥቂ ጋር ተለያይቷል

የጦና ንቦቹን ሰላሳ አምስት ደቂቃዎችን ብቻ ያገለገለው ጋናዊው አጥቂ ከክለቡ ጋር ተለያቷል፡፡

የሳውዲውን ክለብ አልና-ህዳን በክረምቱ በመልቀቅ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ወላይታ ድቻን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሎ የነበረው ጋናዊው አጥቂ ሚካኤል ሳርፓንግ ከወላይታ ድቻ ጋር ቀሪ የዘጠኝ ወራት ኮንትራት እየቀረው ከክለቡ ጋር በጋራ ስምምነት በዛሬው ዕለት መለያየቱን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

እግርኳስን በሀገሩ ጋና ክለቦች ሊቨርቲ ፕሮፌሽናል ድሪምስ ኤፍ በሩዋንዳው ራዩን ስፖርት በታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ እና ያለፈውን ዓመት በሳውዲ አረቢያው ክለብ አልና-ህዳ በመጫወት ቆይታ የነበረው አጥቂው ወላይታ ድቻን በበቂ ሁኔታ ማገልገል ባለመቻሉ በሜዳ ላይ ሰላሳ አምስት ደቂቃዎችን ብቻ ከቆየ በኋላ በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ያጋሩ