ከፍተኛ ሊግ | ሺንሺቾ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ፈፅሟል

የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቶ የነበረው ከንባታ ሺንሺቾ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል።

የ2014 በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ስር ተካቶ የውድድር ዘመኑን በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ሆኖ የፈፀመው እና ተከታታይ ሁለት ዓመታትን ደካማ የውድድር ጉዞን ማድረግ ችሎ ዘንድሮ በፌዴሬሽኑ ለሁለተኛ ጊዜ በከፍተኛ ሊጉ የመቀጠል በለስ የቀናው ከንባታ ሺንሺቾ ዘንድሮ ተጠናክሮ ለመቅረብ ከቀናቶች በፊት የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን ያወጣ ሲሆን በወጣው መሠረትም አሰልጣኝ መኮንን ገላና በበርካቶች ዘንድ ዊሀ በመባል የሚታወቀው አሰልጣኝ በይፋ ቀጥሯል፡፡

የቀድሞው አንጋፋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው መኮንን እግርኳስን መጫወት ካቆመ በኋላ ወደ ሥልጠናው ዓለም በመግባት ባህርዳር ከተማ ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲገባ የአሰልጣኝ ፓውሎስ ጌታቸው ረዳት በመሆን ያሰለጠነ ሲሆን የሀምሞሪቾ ዱራሜ ረዳት አሰልጣኝ በመሆንም ሰርቷል። በአንደኛ ሊጉ ክለብ ጎፋ ባራንቼ እንዲሁም ደግሞ በትውልድ አካባቢው አርባምንጭ ታዳጊዎችን በመሰብሰብ ሲያሰለጥን ቆይቶ አሁን የሺንሺቾ አሰልጣኝ ሆኖ ተቀጥሯል፡፡