ቦሌ ክፍለ ከተማ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው ቦሌ ክፍለ ከተማ የሰባት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል፡፡

ባሳለፍነው ዓመት በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ከታችኛው የሊግ ዕርከን በማደግ ተሳትፎን ያደረገው እና በሜዳ ላይም ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያሳየን የነበረው የአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻው ቦሌ ክፍለ ከተማ ለ2015 የሊጉ ሁለተኛ ዓመት ቆይታው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት በወጣት በተገነባው ቡድኑ ውስጥ ልምድ ያላቸውን ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ዝግጅት ጀምሯል፡፡

በሙገር ሲሚንቶ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ባለፈው ዓመት ጌዲኦ ዲላ ያሳለፈችው አማካዩዋ አዲስ ንጉሴን ጨምሮ ማዕረግ ማቲዮስ ከአርባምንጭ ከተማ እቴነሽ ደስታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሶሊያና ብርሃኔ ከጌዲኦ ዲላ ፣ መኪያ ከድር ከጌዲኦ ዲላ ፣ መንፈስ መቸነ ከአርባምንጭ ከተማ እና ይፍቱስራ ጌታቸው ከለገጣፍ ለገዳዲ የቦሌ አዳዲስ ፈራሚ ናቸው፡፡

ያጋሩ