ከፍተኛ ሊግ | ወልድያ ቡድኑን በማደራጀቱ ቀጥሏል

በቅርቡ ካሊድ መሐመድን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ወልድያ የ11 አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል፡፡

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ያለፈውን ዓመት መሳተፍ ወዳልቻለበት ከፍተኛ ሊግ ውድድር የተመለሰው ወልዲያ ከሰሞኑ ተጠናክሮ ለመቅረብ አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከተለያዩ ክለቦች አዳዲስ አስራ አንድ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም በቀጣይም ከተለያዩ ክለቦች እና በሙከራም ጭምር ለማስፈረም በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

አሁን ከፈረሙት አስራ አንድ ተጫዋቾች መካከል በፋሲል ከነማ ረጅም ዓመታትን በግብ ጠባቂነት ቆይታ የነበረው ቴዎድሮስ ጌትነት ፣ በተመሳሳይ በፋሲል ከነማ እና በድሬዳዋ በአማካይ ስፍራ ላይ ሲጫወት የምናውቀው መጣባቸው ሙሉ ፣ በቡታጅራ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እና መከላከያ የሚታወቀው አማካዩ ቢኒያም ላንቃሞ ፣ በተከላካይ ስፍራ ላይ ለሲዳማ ቡና ፣ ደቡብ ፖሊስ ፣ ነቀምት ከተማ እና አርባምንጭ ያሳለፈው ደረጀ ፍሬው ፣ በመከላከል ሰበታ እና ወልድያ የመስመር ተከላካይ የነበረውን ሙሉቀን ደሳለኝን ጨምሮ ፣ አማኑኤል ቤርባ ተከላካይ ከባቱ ፣ በጋሻው ክንዴ ተከላካይ ቡታጅራ ፣ ፉአድ አቢኖ ተከላካይ ከሀላባ ፣ ሙሴ እንዳለ አጥቂ ከባቱ ፣ ፀጋ ማቲዮስ አጥቂ ከቡታጅራ እና ሱራፌል ከድር አማካይ ከባቱ ከተማ የክለቡ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

ያጋሩ