ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው ሀላባ ከተማ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአምስት ነባሮችን ኮንትራትም አራዝሟል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ዘለግ ያለ የተሳትፎ ታሪክ ያለው ሀላባ ከተማ በየዓመቱ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን መቅረብ ቢችልም ወደ ፕሪምየር ሊግ ዕርከን ለማደግ በተደጋጋሚ ከጫፍ እየደረሰ ሲመለስ አስተውለናል፡፡ ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት በተሻለ ጥንካሬ ለመቅረብ እና ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ውጥን ይዞ እየሰራ የሚገኘው ቡድኑ ከቀናቶች በፊት አሰልጣኝ ራህመቶ መሐመድን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከተለያዩ ክለቦች ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም አምስት በክለቡ የነበሩ ነባሮችን ውልም አራዝሟል፡፡

ክለቡ ያስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች በክሪ መሐመድ ተከላካይ ከዲላ ፣ ሔኖክ ከበደ ተከላካይ ከሰንዳፋ ፣ አዲስ ፈለቀ ተከላካይ ከሰንዳፋ ፣ ኪሩቤል ማርቆስ ተከላካይ ፣ ምስጋና ግርማ አጥቂ ነገሌ አርሲ ፣ አቤል ፋንታ አማካይ ከነገሌ አርሲ ፣ ሞገስ ቱሜቻ ተከላካይ ከደቡብ ፖሊስ እና ፎሴ ሰንቦ አጥቂ አጥቂ ከሰንዳፋ ክለቡን ተቀላቅለዋል፡፡

ቡድኑ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ የሙጃይድ መሀመድ አማካይ ፣ አቡሽ ደርቤ አማካይ ፣ሰኢድ ግርማ አማካይ ፣ አብዱልከሪም ራህመቶ እና ደኘት ዳቆሮን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሷል፡፡

ያጋሩ