በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አዘጋጅነት የሚከወነው የዘንድሮ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀን ይፋ ሆኗል፡፡
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሸን ስር ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2015 የውድድር ዘመን መቼ እንደሚደረግ ፌድሬሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡ የተጫዋቾች የኤም ራ አይ ምርመራ እስከ ህዳር 22 ድረስ ተጠናቆ ከሁለት ቀናት በኋላ ደግሞ ህዳር 24 የዕጣ ማውጣት መርሀግብር ተካሂዶ ውድድሩ ታህሣስ 1 እንዲጀመር መወሰኑን በገፁ አስታውቋል፡፡
ፌድሬሽኑ በተጨማሪም ከውድድሩ ጅማሮ ባለፈ በደንብ ዙርያ ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን በ2015 በልዩ ቴሴራ የተመዘገበ ተጫዋች ወደ ታች ወርዶ ወይም በተመላላሽነት መጫወት እንደማይችሉ ከተገለፀ በኋላ ከ23 ዓመት በታች የሆኑ ተጫዋቾችን በተመለከተ ደግሞ ከዚህ ቀደም ማስመዝገብ የሚቻለው 10 ተጫዋች የነበረ ሲሆን በዘንድሮው የውድድር ዓመት ግን ማስመዝገብ የሚቻለው 5 ተጫዋች ብቻ እንደሆነ እና በአንድ ጨዋታ 3 ተጫዋች ብቻ መሰለፍ እንደሚችሉም መረጃው ያትታል።