የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ጌዲኦ ዲላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ታዳጊዎችንም ከአካባቢው መልምሎ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል፡፡
ከቀናቶች በፊት የቀድሞው አሰልጣኙን ደረጀ በላይ በዋና አሰልጣኝነት ቦታ የቀጠረው ጌዲኦ ዲላ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከወዲሁ ራሱን ለማጠናከር አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስረመ ሲሆን አራት ታዳጊዎችንም ከአካባቢው በመመልመልም የስብስቡ አካል አድርጓል።
ተካልኝ መስፍን አማካይ ከሀላባ ፣ ብሩክ ግርማ ተከላካይ ንግድ ባንክ ፣ ኢሳይያስ ታደሰ አጥቂ ከንግድ ባንክ ፣ ዮሐንስ ኪሮስ አጥቂ ንግድ ባንክ ፣ ሥዩም ደስታ አጥቂ ከጉለሌ ፣ ኦኒ ኡጁሉ አጥቂ ከቤንች ማጂ ቡና ፣ ነቢል ኢብራሂም አማካይ ከኮልፌ ፣ ኤፍሬም ቶማስ አጥቂ ከነገሌ አርሲ ፣ መሐመድ ሻፊ ተከላካይ ወልቂጤ ፣ ፋንታሁን ተስፋዬ ተከላካይ ከሮቤ ከተማ ፣ ሀቲፍ መህዲ ዱከም ተከላካይ ፣ አንዋር አወል አማካይ ከንፋስ ስልክ እና የቀድሞው የወልቂጤ እና የለገጣፎ አማካይ ብስራት ገበየሁ ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚዎች ናቸው፡፡
ክለቡ ከተለያዩ ክለቦች ካስፈረማቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ ቢኒያም ጴጥሮስ ፣ አቤኔዘር ከፍያለው ፣ ኤርሚያስ ተስፋዬ እና መልካሙ ደጀኔ ከአካባቢው ተመልምለው የተያዙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡