ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው ነገሌ አርሲ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ስር ተደልድሎ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ዓመቱን የፈፀመው ነገሌ አርሲ ከቀናቶች በፊት ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ረዘም ያሉ ዓመታትን ክለቡን ያገለገለውን በሽር አብደላን በዋና መንበር ቦታ ላይ ከሾመ በኋላ አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሞ ዝግጅቱን ቀጥሏል፡፡
የቀድሞው የወላይታ ድቻ እና አዳማ ከተማ ተከላካይ ብሩክ ቦጋለ ፣ በአዳማ እና በኤሌክትሪክ ተጫውቶ ያሳለፈው አጥቂው አብዱላኪም ሱልጣንን ጨምሮ ሔኖክ ታደሰ ተከላካይ ከሆለታ ፣ ቴዎድሮስ ታምሩ አማካይ ከሻሸመኔ ፣ ሲሳይ ሚደቅሳ ተከላካይ ከሞጆ ፣ ጌትነት ታዬ ተከላካይ ከሞጆ ፣ ምንተስኖት ተስፋዬ ተከላካይ ከአረካ ፣ ትንሳኤ ኑራ አጥቂ ከሆለታ ፣ ምስጋና ሚልኪያስ አማካይ ከሻሸመኔ ፣ ሮብሰን በዳኔ አማካይ ከሻሸመኔ ከተማ ፣ አብረሃም አለሙ አጥቂ ከጅማ አባቡና እና መስፍን ደገፉ አጥቂ በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡