ፌዴራል ፖሊስ ወደ ቀደመ ዝነኛ ስያሜው ተመልሷል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ክለብ ወደ ቀድሞ ስያሜው መመለሱ ታውቋል።

በአሁኑ ሰዓት በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የእጣ ማውጣት ስነ-ሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ የሊግ እርከን ውድድር የሚሳተፈው ፌዴራል ፖሊስ ደግሞ ወደ ቀድሞ ስያሜው ኦሜድላ መመለሱ በተወካዩ አማካኝነት ተገልጿል።

በ1940ዎቹ የተመሰረተው ኦሜድላ በመጀመርያዎቹ የምስረታ ዓመታት ፖሊስ ሠራዊት በሚል መጠርያ ሲወዳደር ቆይቶ በ1948 ክለቦች የወታደራዊ እና የብሔር ስያሜዎችን እንዲቀይሩ የወጣው ደንብን ተከትሎ ኦሜድላ የሚለውን ስያሜ ይዞ ለረጅም ዓመታት ተወዳድሯል። በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ስር የሚተዳደረው ክለቡ ያለፉትን ዓመታት በፌዴራል ፖሊስ መጠርያነት ሲጠቀም የቆየ ሲሆን አሁን ግን ወደ ቀደመ ገናና ስሙ ተመልሷል።

ያጋሩ