ወደ ከፍተኛ ሊጉ ዳግም ተመልሶ የመሳተፍ ዕድልን ያገኘው ጂንካ ከተማ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአስራ ስምንት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሷል፡፡
ከኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ወደ ከፍተኛ ሊጉ ማደግ ከቻሉ ስምንት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ጂንካ ከተማ ዳግም ወደ ሊጉ በመመለስ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት በአሰልጣኝ መድምም ለገሰ እየተመራ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ሲቀላቅል ከክለቡ የነበሩ አስራ ስምንት ተጫዋቾችን ደግሞ ውላቸውን አድሶላቸዋል፡፡
ከአዳዲስ ፈራሚዎች መካከል የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወንድሜነህ ዓይናለም ወደ ልጅነት ክለቡ ሲመለስ የቀድሞው የአርባምንጭ እና ነቀምት ተከላካይ ዘነበ ተንታን ጨምሮ ፣ ተመስገን ሀንኮ ተከላካይ ከሆለታ ፣ መልካሙ ፉንዱሬ አጥቂ ከጅማ አባ ቡና ፣ ዳዊት ታደለ አጥቂ ከወሊሶ እና ዓለምሰገድ አድማሱ አማካይ ከወሊሶ የክለቡ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
ክለቡ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ የአሸናፊ ኃይለማርያም ፣ ተባረክ ስምዖን ፣ ትንሳኤ ተክሌ ፣ ፍቅሩ አዳነ ፣ ጎሳዬ ብርሀኑ ፣ ኢትዮ ሳንጎሌ ፣ ማኑሄ ጌታቸው ፣ ኑራ ሀሰን ፣ አቤል በላይ ፣ እሱባለው አባይነህ ፣ አንተነህ ተሾመ ፣ ይሁን ትግሉ ፣ ወንድሙ ይታገሱ ፣ ናኩመር በቀለ ፣ ወንድማገኝ አበበ ፣ ዮሴፍ ዲሪባ ፣ በረከት ተስፋዬ እና ማቲያስ ማዳን ውል አራዝሟል፡፡