ከፍተኛ ሊግ | ጅማ አባ ጅፋር ስብስቡን አጠናክሮ ለውድድሩ ተዘጋጅቷል

በቴዎድሮስ ታደሰ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው ጅማ አባ ጅፋር የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና አዳዲስ ተጫዋቾች ቅጥር ፈፅሞ ለውድድሩ ይቀርባል።

የአሰልጣኝ የሱፍ ዓሊ ረዳቶችን በመቅጠር የአሰልጠኞችን አባላትን በማደራጀት ዝግጅታቸውን የጀመሩት አባ ጅፋሮች ለረጅም ዓመታት በክለቡ በግብ ጠባቂ አሰልጠኝ የነበረው መሐመድ ጀማል ወደ ድሬደዋ ከተማ ማቅናቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የጅማ አባ ቡና የግብ ጠባቂ አሰልጠኝ የነበረው ሀብታሙ በቀለን ቀጥረዋል። በምክትል አሰጣኝነት ከዚህ ቀደም በጅማ አባ ቡና እና በሻሸመኔ ከነማ በምክትል እና በዋና አሰላጣኝነት የሰራው ይልማ ሀብቴ አሰላጠኝ የሱፍ ዓሊ ቡድንን በረዳት አሰልጣኝነት ተቀላቅሏል፡፡

በዘንድሮ የውድድር ዘመን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለመመለስ ያለሙት አባ ጅፋች ወደ አስር የሚጠጉ ተጫዋቾችን ሲየስፈርሙ በተከላካይ ስፍራ ላይ ከዚህ ቀደም የቡድኑ አባል የነበረው ዐወት ገ/ሚካኤል ከድሬደዋ ከተማ ፣ ልመንህ ታደሰ ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ ልደቱ ጌታቸው ከመቻል ፣ ዝናው ዘላለም ከዲላ ከተማ ፣ ብሩክ ጌታሁን ኢትዮጵያ መድን ፣ አማኑኤል ጌታቸው ከቡራዩ በአማካይ እና አጥቂ ስፍራ ላይ ደግሞ ናትናኤል በርሄ ከኢትዮጵያ ቡና ፣ ሱራፌል ፍቃዱ ከከፋ ቡና ፣ ዋቁማ ዲንሳ ከነቀምት ከነማ ፣ ብርሀኑ ከጅማ አባ ቡና ክለቡን ተቀላቅለዋል።

በተጨማሪም ጅማ አባ ጅፋሮች በቢጫ ቴሲራ ከከተማው ፕሮጀክቶች ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን ያሳደጉ ሲሆን አምና ከቡድኑ ጋር የነበሩ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችም በስብስቡ ተካተዋል።