የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 0-0 አዳማ ከተማ

👉 “ቢያንስ አንድ ነጥብ እንፈልጋለን ፤ ከመሸነፍ አንድ ይሻላል” ያሬድ ገመቹ


👉 “አንዳንዴ በእግርኳስ ዕድለኛ መሆን ያስፈልጋል” ይታገሱ እንዳለ

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ሀዲያ ሆሳዕና

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ብዙም ፈጣን ጨዋታ አይደለም። በይበልጥ በመከላከል ላይ የተጫወትንበት ምክንያት ብዙ ተጫዋቾች በህመም እና በተለያየ ጉዳዮች ጎድለውብን ወጣቶቹን ተጫዋቾች አሰልፈን ነው የገባነው። ስለዚህ አንድ ነጥብ ለእኛ አስፈላጊያችን ነው፡፡

የግብ ዕድል ስላለመፍጠራቸው…

አዎ! ወሳኝ ወሳኝ ቦታ ላይ ያሉ ተጫዋቾች ናቸው በህመም የወጡብን። በተጨማሪ ደግሞ ድነውም የተመለሱ ተጫዋቾች በጨዋታ ውስጥ አልገቡም ፤ ገና አላገገሙም። ካለብን ችግር አንፃር የግድ ስለሆነብን ነው የተጠቀምናቸው፡፡

አቻ ውጤትን ስለመፈለጋቸው…

ቢያንስ አንድ ነጥብ አዎ እንፈልጋለን ፤ ከመሸነፍ አንድ ይሻላል፡፡ ምክንያቱም ወደ ላይ ስላለን ቢያንስ እንዳንርቅ ያደርገናል፡፡

አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ – አዳማ ከተማ

ስለ ጨዋታው…

የሚሳቱ ኳሶች እየታዩ ነው። አንዳንዴ በእግርኳስ ዕድለኛ መሆን ያስፈልጋል። እንቅስቃሴው ከመጀመሪያው ጀምሮ አጥቅተን ነው የተጫወትነው ፤ ተጫዋቾችም ያላቸውን ነገር ከፍለዋል። ዛሬ ውጤቱ ይገባናል ብዬ የማስበው ጨዋታ ነበር።

ድል ስላላሳኩበት ምክንያት…

ከተጫዋቾቹ ጋር ተያይዞ ያለንበት ቦታ በጣም እንዲጓጉ ያደርጋቸዋልና ኳሶች ይሳታሉ ፤ ትንሽ መረጋጋት ይፈልጋል እንጂ አብዛኛውን በማጥቃት ነው የተጫወትነው። አጨራረስ ላይ ትንሽ መረጋጋት ይፈልጋልና እሱን ነገር ማስተካከል ነው።

ስለተጋጣሚያቸው…

ሀዲያ ትልቅ ቡድን ነው። ጎበዝ አሰልጣኝ አላቸው፣ ውጤታቸው ጥሩ ነው። ከላይ ከአንድ እስከ አምስት ያለ ቡድን ነው በምንም መልኩ ቀለል አድርገን ልንገባ አንችልም። እንኳን ለእነሱ ከእኛ በታች ለነበረው ለገጣፎ ትልቅ ትኩረት ይዘን ነው የምንመጣው። አንዳንዴ ውጤቱና የሚጫወቱት ጨዋታ ማይገልጻቸው ቡድኖች አሉ። ለሁሉም ቡድኖች እኩል ትኩረት ነው የምንሰጠው ፤ ሌላ የተለየ ነገር የለም።