የአሰልጣኞች አስተያየት | ለገጣፎ ለገዳዲ 1-1 አርባምንጭ ከተማ

👉”ሊጉ እንደ ጠበቅነው አይደለም ፤ እንደ ገመትኩትም አይደለም። እኔም መጀመሪያ የነበሩት አመራሮችም በጣም አቅልለነው ነበር” ጥላሁን ተሾመ

👉”መውሰድ የሚገባንን ነገር አጥተናል ፤ ነጥቡን ይዘን መውጣት ነበረብን። መታረም እና መስተካከል ያለበት ነገር አለ” መሳይ ተፈሪ

አሰልጣኝ ጥላሁን ተሾመ – ለገጣፎ ለገዳዲ

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታውን ለማሸነፍ በጣም ጥረን ነበር፡፡ አቻውን ውጤት በጣም ባለቀ ሰዓት ነው ያገኘነው። ደስ ብሎኛል ፤ ጥሩ ነው፡፡

በዛሬው ጨዋታ የአዲሱ አሰልጣኝ ሚና ስለ መኖሩ…

አዎ አለበት! ድጋፍ አለበት። ትክክለኛ ድጋፍ አለበት። የተሻለ መነሳሳት ፈጥሯል። ጥሩ ነገር አለ፡፡

ስለ መጨረሻው የዋና አሰልጣኝነት ሚናው…

ብዙ ነጥቦች አላመጣውም ስለዚህ ቦርዱ ወስኗል፡፡ ይሄ ውሳኔ ደግሞ አግባብ እና ትክክለኛ ነው። ለውጥ ይፈለጋል ፤ በምክትልነት ሰራለሁ ሥራዬን አክብሬ ፈቅጄ እሰራለሁ፡፡

ስለ ሊጉ…

ሊጉ እንደ ጠበቅነው አይደለም። እንደ ገመትኩትም አይደለም። እኔም መጀመሪያ የነበሩት አመራሮችም በጣም አቅልለነው ነበር። በዚህ ተነስተን ብዙ እንድናጣ አድርገናልና ልምድ ይፈልጋል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ

ስለ ጨዋታው…

ጎሎችን ቶሎ ለማስቆጠር ነበር አቅደን የገባነው። በጊዜ ጎል አስቆጥረናል ፤ የጎል አጋጣሚዎችንም ስንፈጥር ነበር። በአጠቃላይ መውሰድ የሚገባንን ነገር አጥተናል ፤ ነጥቡን ይዘን መውጣት ነበረብን። መታረም እና መስተካከል ያለበት ነገር አለ።

በመጨረሻ ደቂቃ ስለተቆጠረባቸው ግብ እና ስለ ቡድናቸው እንቅስቃሴ…

የእኛ ድክመት ነው። ማሸነፍ መቻል አለብን። እንቅስቃሴው ማደግ አለበት። ከዚህ በተሻለ መንቀሳቀስ አለብን። ተረጋግተን የግብ ዕድሎችንም ስንፈጥር ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ መጨረስ ይፈልጋል እነዚህን ነገሮች ማረም አለብን።

ክፍተት ስላዩበት ቦታ…

በእርግጥ ጎሎችን በተከታታይ እያስቆጠርን ነው። ባለፈው ሁለት ዛሬ አንድ ግብ አስቆጥረናል። ቀድመን ያገባናቸውን ጎሎች ማስጠበቅ መቻል አለብን ፤ በራስ መተማመናችን ከዚህ በላይ ማደግ አለበት።