የአሠልጣኞች አስተያየት | ለገጣፎ ለገዳዲ 3-4 ወላይታ ድቻ

“የድሬዳዋ ቆይታችን በጣም ጥሩ ነበር” ፀጋዬ ኪዳነማርያም

“በሰላም ውድድራችንን ጨርሰናል። ውጤቱ ግን በጣም አስከፊ ነው ፤ አንገት የሚያስደፋ ነው” ጥላሁን ተሾመ

ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ወላይታ ድቻ

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታውን በሁለት መልክ ነው መግለፅ የሞችለው። በመጀመሪያ ተጋጣሚያችን በጎል መምራት የሚችልበት አጋጣሚ አጋጥሞናል። ይሄ እንደሚያጋጥም ገምተናል ምክንያቱም በነፃነት ነው የሚጫወቱት። እኛ ደግሞ ከባህርዳር ከመጣን በኋላ እዚህ መጥተን ብዙ ነገር ለማስተካከል ሞክረናል። ይሄ የዛሬ ማሸነፍ ደግሞ በቀጥታ አንድ ጨዋታ እየቀረን ወደ አምስተኝነት የሚወስደን ስለነበረ እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ነበረ የተነጋገርነው ግን ከሚገርመው ነገር ለገጣፎ በየትኛውም መንገድ ጎል ከገባባቸው በኋላ ብዙ ይወርዳሉ እንጂ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በጣም ታታሪ ናቸው። ልምድ ያላቸው በየቦታው አሉና ጥሩ ቡድን ነው። አስራ ስድስተኛ ሆኖ የመጣ ስለሆነ ቢያንስ ወደ አስራ አምስተኛ ለመምጣት የሚያስብበት ሁኔታ ስለነበሮ በጣሞ ፈታኝ ቡድን እንደሚያጋጥመን ገምተናል። እንደተባለውም በተለይ በመጀመሪያው አርባ አምስት ደቂቃ በጣም ፈትኖናል ፤ በሁሉም ነገር ፈትነውናል። በእኛ ቡድን ላይ ጉጉት ትንሽ ይታይ ነበር። መጀመሪያ አርባ አምስት ደቂቃ በቡድናችን ላይ መነቃቃት አልነበረም። በሁለተኛው አጋማሽ ግን የተለያዩ ቅያሬዎችን አድርገን ውጤታማ ሆነናል። እንደ አጠቃላይ የድሬዳዋ ቆይታችን በጣም ጥሩ ነበር። አምስት ጨዋታዎችን አሸንፈናል ሁለት አቻ ወጥተናል አንድ በጊዮርጊስ ተሸንፈናል። አጠቃላይ እዚህ ድሬዳዋ ከገባን በኋላ ይሄን ነጥብ አምጥተናልና የበለጠ አሁን በጣም ጥሩ ላይ ነን። በተረፈ ግን እኛ ከዚህ በኋላ እጅግ በጣም ጥሩ ሆነን ነው መገኘት የሚጠበቅብን።

ስለ ቀጣዩ ዕረፍት…

ከምንም የበለጠ የሚጠቅመን የተጎዱ ተጫዋቾች ያገግማሉ ፤ እያገገሙ ያሉ ልጆች አሉ። የበለጠ የተሻለ በጉዳት ቡድኑን ያልተቀላቀሉ ተጫዋቾች አሉ። እነርሱ ይደርሳሉ ብለን ነው የምናስበው። በተረፈ እነዚህ ወጣት ተጫዋቾች ናቸው ብዙ ቡድኑን እየታደጉ ያሉት ነባሩም እያደባለቅን ያለነውና የግድ ነው ሌላ አማራጮች ስለሌሉ። በስልጠና ማብቃት ነው። አሁን ወጣቶች ሜዳውን እየደፈሩ ነው ያሉትና በስልጠና እያበቃን በወዳጅነት ጨዋታ እያበቃን የተወሰነ አንድ አስር ቀን ዕረፍት ሰጥተን ከእዛ ሶዶ ገብተን ወደ ዝግጅታችንን እንገባለን። ከፈጣሪ ጋር ቀሪ ጨዋታዎችን ደግሞ እያንዳንዱ ነገሮች ላይ ሰርተን እንመጣለን።

ጥላሁን ተሾመ – ለገጣፎ ለገዳዲ

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ጥሩ ነበር። በፊት መስመራችን በተሻለ ሁኔታ ከሌላው ጊዜ የጎል ዕድሎችን ፈጥረናል ፤ ጎልም ማግባት ችለናል። በተቃራኒው ደግሞ የኋላ መስመራችን በጣም በጣም ዋጋ አስከፍሎናል።

እየመሩ ስለ መሸነፋቸው…

አንድ ለባዶ ስንመራ ነበር። ከእዛ በኋላ አቻ ሆንን መራን አገቡብን መልሰን አገባን መከላከል ላይ በጣም ክፍተት ነበረብን መረጋጋት አልቻሉም ፤ በእዛም ተሸንፈናል።

ስለ ድሬዳዋ ቆይታ…

እግዚአብሔር ይመስገን ፤ በሰላም ውድድራችንን ጨርሰናል። ውጤቱ ግን በጣም አስከፊ ነው አንገት የሚያስደፋ ነው።

ስለ ቀጣዩ ረጅም ዕረፍት…

የተጀመረ ቦርዶች የሚሰጡን ስራዎች አሉ። የአሰልጣኝ ቅያሪም በእንጥልጥል ነው ያለው እሱም እልባት አግኝቶ ተጫዋቾችም ቀያይረን የተሻለ ነገር ለመስራት ዝግጁ ነን።