የፕሪሚየር ሊጉ የበላይ አካል ሲምፖዚየም አዘጋጅቷል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከአንድ ዓመት በላይ በፈጀ ጊዜ ያስጠናውን ጥናት የሚያቀርብበት የሲምፖዚየም መድረክ አዘጋጅቷል።

ከሦስት ዓመታት በፊት በሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ውድድራቸውን ራሳቸው ለመምራት ያቋቋሙት አክሲዮን ማኅበር በየጊዜው ራሱን እያጠናከረ መምጣቱ ይታወቃል። ማኅበሩም የሊጉን የሥያሜ እና ምስል መብት ዳጎስ ባለ ገንዘብ በመሸጥ ክለቦች ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኙ ማድረጉ ይታወቃል። ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ወቅቶች ስልጠናዎችን ሲሰጥ የነበረው ማኅበሩ አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት በላይ በፈጀ ጊዜ እርግኳሱ ላይ ያስጠናውን ጥናት ለባለድርሻ አካላት እንዲቀርብ ሲምፖዚየም አዘጋጅቷል።

\"\"

በታውሰን ዩኒቨርስቲ የስፖርት ማኔጅመንት መምህር በሆኑት እና በአሜሪካ በሚገኙ የስፖርት ድርጅቶች ውስጥ በአማካሪነት በሚሰሩት እንዲሁም በተጓዳኝ ሪሰርቸር በሆኑት ዶ/ር ጋሻው አበዛ የተጠናው ይህ ጥናት ‘ዘርፈ ብዙ የግምገማ ጥናት እና የልማት ፍኖተ ካርታ\’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣዩ ሳምንት ጥር 3 እና 4 የሀገሪቱ ከፍተኛ የስፖርት እና የእግርኳስ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል እንደሚቀርብ ተጠቁሟል።

\"\"