ዓለም አቀፋ የእግርኳስ አስተዳዳሪ አካል የሆነው ፊፋ ኢትዮጵያዊያን የ2023 ኢንተርናሽናል ዳኞችን ዝርዝር በሁለቱም ፆታዎች ይፋ አድርጓል።
በ2023 በኢንተርናሽናል ዳኝነት ኢትዮጵያን ወክለው በሁለቱም ፆታዎች በዳኝነት እንዲያገለግሉ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አማካኝነት ፈተና ተሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። በሲኒየር ደረጃ እንዲሁም በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ፈተናቸውን ወስደው ስማቸው ለፊፋ በተላከው መሠረትም ኢትዮጵያን የሚወክሉ የ2023 ዳኞች እነማን እንደሆኑ አሁን ታውቀዋል።
ለረጅም ዓመታት በኢንተርናሽናል ረዳት ዳኝነት በሀገር አቀፍ እና በአህጉራዊ የተለያዩ ውድድሮች ላይ ያገለገለው ክንዴ ሙሴ ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ሳይካተት ሲቀር ሌላኛው ረዳት ዳኛ ሸዋንግዛው ተባበል ከዳኝነት ራሱን በማግለሉ እንዲሁም ባሳለፍነው ዓመት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በመሆን ያገለገለችው ምስጋና ጥላሁን ከፈተና ጋር በተገናኘ ስማቸው ሳይካተት ቀርቷል። በምትኩም ፊፋ በወንድ ረዳት ዳኝነት አበራ አብርደውን እና ሙስጠፋ መኪን በሴት ዋና ዳኝነት ሲሳይ ራያን ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም አቀፍ ዳኝነት ክብርን አግኝተዋል።
ኢትዮጵያዊ ዳኛ በአምላክ ተሰማ ከዳኝነት በተጨማሪ የቫር ዳኝነት ዝርዝር ውስጥም ስሙ የተካተተ ዳኛ ሆኗል።
የየ2023 አለም አቀፍ ዳኞች ዝርዝር
ዋና ወንድ ዳኞች
1 በአምላክ ተሰማ
2 በላይ ታደሰ
3 አሸብር ሶበቃ
4 ቴዎድሮስ ምትኩ
5 ለሚ ንጉሴ
6 ማኑሄ ወልደፃዲቅ
7 ሀይለየሱስ ባዘዘው
ሴት ዋና ዳኞች
1 ሊዲያ ታፈሰ
2 ፀሐይነሽ አበበ
3 ሲሳይ ራያ (አዲስ)
4 መዳብ ወንድሙ
ረዳት ወንድ ዳኞች
1 አበራ አብርደው (አዲስ)
2 ትግል ግዛው
3 ሙስጠፋ መኪ (አዲስ)
4 ተመስገን ሳሙኤል
5 ፋሲካ የኋላሸት
6 ይበቃል ደሳለኝ
ረዳት ሴት ዳኞች
1 ወይንሸት አበራ
2 ይልፋሸዋ አየለ
3 ብርቱካን ማሞ
4 ወጋየሁ ዘውዱ