ቻን | ቅዳሜ ዋልያዎቹን የምትገጥመው ሞዛምቢክ ዛሬ የመጨረሻ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ታደርጋለች

በቻን ውድድር ከሀገራችን ጋር የተደለደለችው ሞዛምቢክ በዛሬው ዕለት በደንብ አቋሟን የምትፈትሽበትን ፍልሚያ ለማድረግ ተዘጋጅታለች።

\"\"

የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የቻን ውድድር ከቀናት በኋላ በአልጄሪያ እንደሚከናወን ይታወቃል። በዚህ ውድድር የሚሳተፉት 18 ብሔራዊ ቡድኖችም የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅታቸውን እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከሞሮኮ ጋር ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን አድርጎ በነገው ዕለት ወደ ውድድሩ ስፍራ ለማምራት እየተሰናዳ ይገኛል። ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ 1 የተደለደለችው ሞዛምቢክ ቀድማ አልጄሪያ በመከተም ልምምዷም ስትሰራ የነበረ ሲሆን ከሁለት የሀገሩ ክለቦች ጋርም ተጫውታ አቋሟን ፈትሻለች።

\"\"

በአሠልጣኝ ቼኪኒዮ ኮንዴ የሚመራው የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን \’ጠንከር ያለ የወዳጅነት ጨዋታ ሳይከውን ውድድሩን ሊጀምር ነው\’ የሚል ስጋት ሲሰማ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ከጠንካራዋ ጋና ጋር የመጨረሻ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ መያዙ ተሰምቷል።

ከቀናት በፊት ጋና ከሌላኛዋ በዚህ ምድብ የምትገኘው አልጄሪያ ጋር ጨዋታ አድርጋ ያለ ግብ 0-0 መለያየቷ ይታወሳል።