\”ኳስ የቅንጦት እቃ ነው?\” አቶ ባህሩ ጥላሁን

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ያዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ሐላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በስፍራው ለተገኙ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ከኳስ ጋር የተገናኘ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከተመሰረተ ሦስት ዓመት የሞላው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አንድ ዓመት ተኩል በፈከ ጊዜ ያስጠናውን ጥናት በዛሬው ዕለት ለእግርኳሱ ባለ-ድርሻ አካላት የሚቀርብበት ሲምፖዚየም እየተከናወነ ይገኛል። ጥናቱ ከመቅረቡ ቀደም ብሎ የዕለቱ የክብር እንግዶች የመክፈቻ ንግግር በሚያደርጉበት ጊዜ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በንግግራቸው መሐል ያነሱት ሀሳብ ትኩረትን ስቧል።

\"\"

ከወራት በፊት መንግስት ላልተወሰነ ጊዜ የውጪ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጪ የሚገቡ ዕቃዎችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ የሚገኘውን ኳስ በተመለከተ የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ በአዳራሹ የመንግስት ተወካዮች በመገኘታቸው የውጪ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ዕቃዎች መካከል ኳስ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው በዝርዝሩ ላይ የኳሱ አይነት የፑል፣ የመረብ፣ የከረንቡላ፣ የእግር ወይስ ሌላ እንደሆነ በግልፅ እንዳልተቀመጠ በማንሳት አሁን ያሰባሰባቸው እግርኳስ ግን \”የቅንጦት እቃ\” በመባል መፈረጅ እንደሌለበት እና በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሊግ እርከን የሚገኙ ቡድኖች እግዱ ከመጣሉ በፊት በገቡ ኳሶች ብቻ እየተጫወቱ እንደሆነ አንስተው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ በሀገሪቱ የመጫወቻ ኳስ እጥረት ሊከሰት ስለሚችል ጉዳዩን መንግስት እንዲያጤነው መልዕክት አስተላልፈዋል።

\"\"