ቻን | \”ሞዛምቢክን ማሸነፍ ይገባን ነበር\” መስዑድ መሐመድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ያለግብ ከተለያየ በኋላ የቡድኑ አምበል መስዑድ መሐመድ የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰጥቷል።

በቻን የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ ጋር ትናንት አመሻሽ ጨዋታውን አድርጎ በአስቆጪ ሁኔታ 0ለ0 ተለያይቷል። በጨዋታው በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ በርካታ ግልፅ የግብ ማግባት አጋጣሚዎችን ፈጥሮ የነበረው ዋልያው ሦስት ነጥብ ሳያሳካ መውጣቱ በብዙዎች ዘንድ ቁጭትን የፈጠረ ሲሆን የቡድኑ አምበል መስዑድ መሐመድም ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ማሸነፍ ይገባቸው እንደነበር ተናግሯል።

\"\"

\”ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል። የመጀመሪያ ጨዋታችንን ለማሸነፍ የተቻለንን ሁሉ አድርገናል ፤ ማሸነፍም ይገባን ነበር። ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ቀሪዎቹን ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ለማሸነፍ እንጥራለን።\” በማለት ሀሳቡን ከሰጠ በኋላ ከቀጣዩ የአልጄሪያ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ተከታዩን ብሏል።

\”አልጄሪያ በደጋፊዎቿ ፊት እንደመጫወቷ ፈተናው ከበድ ይላል። አሁን ግን ከጨዋታው (ከሞዛምቢኩ) እረፍት አድርገን ለአልጄሪያው ጨዋታ ዝግጅታችንን መጀመር ነው ያለብን።\” የሚል አጠር ያለ ንግግሩን አሰምቷል።

\"\"

የሞዛምቢኩ ተከላካይ አማድ ሞሐመድ በበኩሉ በመጀመሪያው አጋማሽ ቡድናቸው ጥሩ እንዳልነበር አምኖ በሁለተኛው አጋማሽ ግን የተሻለ ለመንቀሳቀስ እንደሞከሩ ሲናገር ተደምጧል። በቀጣዩ የሊቢያ ጨዋታ ድል አድርገው አልጄሪያን የምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ለመግጠም ሀሳብ እንዳላቸውም ገልጿል።