ከባህልና ስፖርት ሚኒስተር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ጋር የተደረገ ቆይታ…

👉 “ግንባታው ቆሟል መዘገየትም እየታየ ነው። ለመዘግየቱ ብዙ ምክንያቶች አሉ…

👉 “ይህን ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማድረግ እየተረባረብን ነው…

በባህልና ስፖርት ሚኒስተር አማካኝነት የካፍን መስፈርት በሚያሟላ መልኩ የማሻሻያ ሥራው ከሁለት ዓመት በፊት የጀመረው የአዲስ አበባ ስታዲየም አስቀድመን ባጋራናቹ መረጃ መሠረት የመጫወቻ ሜዳው፣ የመልበሻ ክፍሉ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግናባታ መጠናቀቅ ችሏል። ሆኖም ቀሪ ሥራዎች የተመልካች መፀዳጃ ቤቶች ፣ የኤሌክትሪክ እና የሳኒተሪ ሥራዎችን አለመካሄዳቸውን እና ከአራት ወር በፊት ግንባታው መቆሙን ገልፀን ነበር። በጉዳዩ ዙርያ ማብራሪያ እንዲሰጡን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት የሰጡንን ማብራሪያ እንዲህ አቅርበነዋል።

\"\"

“ግንባታው ቆሟል መዘገየትም እየታየ ነው። ለመዘግየቱ ብዙ ምክንያቶች አሉ መንግሥትም ሥራው በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ቢያስብም ገና ከግናባታው ጅማሮ አንስቶ መታየት የነበረባቸው አንዳንድ ችግሮች አጋጥመውናል። ለምሳሌ ግንባታውን የወሰደው ኮንትራክተሩ 365 ቀን ቢወስድም ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዘግይቶ (ከሁለት ወር በኋላ) ነው ሥራውን የጀመረው። ሌላው ትልቁ ጉዳይ የመጫወቻው ሜዳ ሳር ነው። ግንባታው ከተጀመረ በኋላ ኢትዮጵያ ሳሩን አትሰራውም። ካፍም ፊፋም አይቀበለውም የሚል ክርክር ተነስቶ። \’እንዴት የማይቀበሉን ከሆነ እንሰራለን ?\’ በሚል አመንትተን በማሰብ የሳር ተከላው እንዳይጀመር አቆምነው። በዚህም ምክንያት ከሁለት ወር በላይ ተጨማሪ ባከነ። በኋላ ሳሩ በእኛ አቅም መሰራት እንደሚችል በማመን ደፍረን ገባን አሁን የምታዩትን ጥሩ ሳር መስራት ተችሏል።

ሌላው በዲዛይን ወቅት ያልታዩ ችግሮች ተከስተውብናል። የስታዲየሙ ጥላ ፎቅ ግንባታው ካለቀ በኋላ የቆየ እንደመሆኑ መጠን የማፍሰስ ሁኔታ አጋጥሞናል። በአጠቃላይ ሌሎች መክንያት ተደምሮ ግንባታው ሊዘገይ ችሏል። አሁን ግን አጣድፈን ለመጨረስ ጥረት እያደረግን ነው። በመጀመርያው ምዕራፍ ያልተሰሩ ቀሪ ሥራዎች ስላሉ ከመንግሥት የበጀት ጥያቄ አቅርበን ተፈቅዶልናል። ያው ያቆምከውን ሥራ ዝም ብለህ አትጀምረውም። በድጋሚ ጨረታ አውጥተናል። ቴክኒካሊ ነገሮች አልቀው ከገንዘብ ጋር የሚገናኘውን አንዳንድ ውድድሮችን ጨርሰን በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታውን አውጥተን ሥራ እንጀምራለን። እናውቃለን ከፊት ለፊታችን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር ያደርጋል። ይህን ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማድረግ እንሯሯጣለን። በእኛ እምነት መጋቢት 17 ይመስለኛል ጨዋታው ለዛ የሚደርሰውን ምዕራፍ በመጨረስ በቀጣይ ቀሪ ሥራዎችን ለመስራት እናስባለን። በፍጥነትም ለማጠናቀቅ ጥረት እናደርጋለን። እንደሚታው የቀረው ነገር ብዙም አሳሳቢ አይደለም። ልተገምተው ከምትችለው በላይ አብዛኛዎቹ ሥራዎች ተሰርተዋል። ስለዚህ ብዙም የሚያሳስብ አይደለም።” በማለት ሀሳባቸውን አጋርተውናል።

\"\"