ዐፄዎቹ የመስመር ተጫዋች አስፈርመዋል

ከቀናት በፊት አዲስ አሠልጣኝ የሾመው ፋሲል ከነማ በዛሬው ዕለት የመስመር ተጫዋች የግሉ አድርጓል።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፉት ፋሲል ከነማዎች ከኃይሉ ነጋሽ ጋር ከተለያዩ በኋላ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝ እያሱ መርሀፅድቅን በረዳት አሰልጣኝነት በመቅጠር በቀጣይ ከአዳማ ጀምሮ ለሚደረገው የሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች ማረፊያቸውን አዲስ አበባ ሆሊዴይ ሆቴል በማድረግ ዝግጅታቸውን የቀጠሉ ሲሆን ቡድኑን ለማጠናከርም አዲሱ አሰልጣኝ ከዚህ ቀደም በአዳማ እና ሀድያ ሆሳዕና ያሰለጠኑትን የመስመር አጥቂ ዱላ ሙላቱን በይፋ የመጀመሪያ ፈራሚ ማድረጋቸውን በተለይ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

እግር ኳስን በነቀምት ከተማ ከጀመረ በኋላ ለደቡብ ፖሊስ ፣ መቐለ 70 እንደርታ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ አዳማ ከተማ እንዲሁም ካለፈው ዓመት ጀምሮ በፕሪምየር ሊጉ እና እስከ ዘንድሮው የውድድር ዓመት አጋማሽ ድረስ በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ጅማ አባጅፋር ሲጫወት የሰነበተው ተጫዋቹ ከቀድሞው አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለ ጋር ዳግም ለመስራት ፋሲልን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሏል።

ያጋሩ