ሲዳማ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረሟል

በዝውውር ፍፃሜው ዕለት ሲዳማ ቡና ከሀገር ውስጥ ተከላካይ ከሀገር ውጪ ደግሞ አጥቂ ማስፈረም ችሏል።

\"\"

በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ የሚመራው ሲዳማ ቡና በሁለተኛው ዙር የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ አለብኝ ባለው ክፍተት ላይ ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ከፈረሰኞቹ ጋር በስምምነት የተለያየውን የመስመር እና የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ደስታ ደሙ እና ጋናዊውን አጥቂ ፒሊፕ አጃህን በአንድ ዓመት ውል ማስፈረሙን ክለቡ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ደስታ ደሙ የመጀመሪያው የክለቡ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል። የቀድሞ የሙገር ሲሚንቶ ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ደደቢት ተጫዋች 2012 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመቀላቀል ያለፉትን አራት የውድድር ዓመታት ከክለቡ ጋር ቆይታ ነበረው። በመሐል እና በመስመር ተከላካይ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለው ደስታ ከፈረሰኞቹ ጋር ቀሪ የውል ዕድሜ እየቀረው በስምምነት በመለያየት የክለብ ህይወቱ አምስተኛ አድርጎ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል።

\"\"

ጋናዊው የ25 ዓመት አጥቂ ፒሊፕ አጃህ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ሲዳማ ቡናን በይፋ መቀላቀል ችሏል። 1 ሜትር ከ81 የሚረዝመው እና አብዛኛዎቹን የእግር ኳስ ህይወቱን በህንዶቹ ክለቦች ሞሀመዳን ፣ ካልክ ከስተምስ ፣ ኔሮካ ፣ ባሀዋኒፖር ፣ ጎ ኩላም እና ጋር-ሀዋል በተባሉ ቡድኖች ውስጥ ከቆየ በኋላ ወደ ባንግላዲሽ አምርቶ እስከ ህዳር ወር ድረስ ራማታጃኒ ለተባለ ክለብ ግልጋሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ ማረፊያው ሲዳማ ቡና ሆኗል።
\"\"