በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመራው አርባምንጭ ከተማ በዝውውሩ ሁለተኛ ፈራሚውን አግኝቷል።
በፕሪምየር ሊጉ ላይ በሁለተኛው ዙር በርካታ ለውጦችን አድርገው ይቀርባሉ ተብለው ከሚጠበቁ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው አርባምንጭ ከተማ እስካሁን የአህመድ ሁሴንን ውል አራዝሞ አበበ ጥላሁንን በአዲስ መልክ ካስፈረመ በኋላ ሌላኛው ፈራሚው በማድረግ ከከፍተኛ ሊጉ ቤንች ማጂ ቡና ዮሐንስ ተስፋዬን የግሉ አድርጓል።
ከሀረር ሲቲ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ ከተገኘ በኋላ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ባቱ ከተማ እና ዘንድሮ በቤንች ማጂ ቡና ያሳለፈው ወጣቱ ተከላካይ ዮሐንስ በአንድ ዓመት ውል የአዞዎቹ አዲሱ ተጫዋች ሆኗል።