የትግራይ ስታዲየም አሁናዊ ሁኔታ…

የትግራይ ስታዲየም እንደሌሎች የክልሉ መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል።

\"\"

ለሦስት ዓመታት ከተካሄደው አውዳሚ ጦርነት በፊት በሀገሪቱ ውስጥ ከነበሩ እና ለጨዋታ ምቹ ከሆኑ ስታዲየሞች መካከል አንዱ የነበረው የትግራይ ስታዲየም እንደሌሎች የክልሉ መሰረተ ልማቶች ቀላል የማይባል ውድመት ደርሶበታል። ባለፉት ዓመታት የፕሪምየር ሊግ እና የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ያስተናገደው ይህ ስታዲየም በ2009 የሳር ተከላው በ2010 አጋማሽ ደግሞ የመሮጫ መም ሲሰራበት ከዋና ሜዳው ውጭም ሦስት ደራጃቸው የጠበቁ የልምምድ ሜዳዎች ፣ ሦስት ግንባታቸው ያላለቁ የ \” Outdoor \” ሜዳዎች የነበሩበት ስታዲየም ነው። ነገር ግን በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት የመልበሻ ቤቱ እና የመሮጫ መሙ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

የክልሉ ስፖርት ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ በስታዲየሙ የደረሰውን ውድመት በማጥናት ላይ ሲገኝ ጥናቱ ከተገባደደ በኋላም ማብራርያ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል። ሜዳው የኮሮና ወረርሺኝ ከመከሰቱ በፊት የካቲት 17 2012 መቐለ 70 እንደርታ እና ባህዳር ከተማ ያካሄዱትን ጨዋታ ለመጨረሻ ግዜ ማስታናገዱ ይታወሳል።

\"\"

በ1990\’ዎቹ ግንባታው የጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታው ሂደት የዘገየው ስታዲየሙ ባለፉት ዓመታት መቐለ 70 እንደርታ ፣ ወልዋሎ ዓድግራት ዩንቨርስቲ እና ስሑል ሽረ ሲገለገሉበት ቆይተዋል። በቻን ውድድርም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ማስተናገዱ ይታወሳል።