ጋናዊው አጥቂ ከጣና ሞገደኞቹ ጋር ተለያየ

ባህርዳር ከተማ ጋናዊውን አጥቂ በዲሲፕሊን ምክንያት ውሉን በማቋረጥ አሰናብቷል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ዘለግ ያለ ቆይታን ካደረጉ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የጋና ዜግነት ያለው የፊት መስመር አጥቂው ኦሴ ማውሊ ተጠቃሹ ነው።

\"\"

የጋናውን ክለብ አሻንቲ ኮቶኮን ከለቀቀ በኋላ በፋሲል ከነማ ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሰበታ ከተማ እንዲሁም ደግሞ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በባህርዳር ከተማ እየተጫወተ አምስተኛ ዓመቱን ያስቆጠረው ይህ አጥቂ ከባህርዳር ጋር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ኮንትራት የነበረው ቢሆንም ክለቡ ተጫዋቹን በዲሲፕሊን ውል በመቅደድ አሰናብቼዋለሁ ብሏል።

ክለቡ እንዳለው ከሆነ አጥቂው ከተጨዋቾች ጋር በተደጋጋሚ በሚፈጥራቸው ችግሮች የተነሳ በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች ቢደርሱትም ከጥፋቱ ሊማር ባለመቻሉ እና ጨዋታ እየመረጠ በመጫወት ከክለቡ ውጤት ይልቅ የራሱን ጥቅማጥቅም ማስቀደም ፣ የቡድኑን ተጫዋቾች አፅያፊ ስድብ መሳደብ እና ለጥል መጋበዝ አልፎም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የክለቡ ደጋፊዎች በመሳደቡ ከድርጊቱ መማር ባለመቻሉ ክለቡ የተጫዋቹን ውል በማቋረጥ አሰናብቶታል።

\"\"