\”ለተመዘገበው ውጤት ይቅርታ እንጠይቃለን\” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ቆይታ ዙሪያ እየተሰጠ ባለው መግለጫ ላይ ዋና አሰልጣኙ ውበቱ አባተ ኃላፊነቱን በመውሰድ ይቅርታ ጠይቀዋል።

\"\"

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በመከናወን ላይ ባለው የዘንድሮው የቻን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ ሳያልፍ መቅረቱ ይታወሳል። በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የነበረው ልዑክ በበረራ እጥረት ዘግየት ብሎ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰ ሲሆን ዛሬ በእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ስለአጠቃላይ ቆይታው መግለጫ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

መግለጫው በፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና በዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተሰጠ ነው። በዚሁ መግለጫ ላይ አሰልጣኙ ባቀረቡት ማብራሪያ ላይ በተመዘገበው ውጤት ማዘናቸውን እና ለዚህም ኃላፊነቱን በመውሰድ ይቅርታ እንደሚጠቁ በይፋ ተናግረዋል።

\"\"