የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር ቀጥሯል

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ለመቅጠር የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን መስፈርቱን ያሟሉ አምስት ተወዳዳሪዎችም ባለፈው ሳምንት በጁፒተር ሆቴል ለውድድር የቀረበውን የአንድ ዓመት የእግር ኳስ ልማት እቅድ አዘጋጅተው ገለፃ አድርገው ነበር።

\"\"

የፊፋ የቴክኒክ አማካሪ ዶሚኒክ ኒዮንዚማ በተገኙበት የተደረገውን ገለፃ ጨምሮ በስድስት የተለያዩ መመዘኛዎች (የስራ ልምድ ፣ የአሰልጣኝነት ላይሰንስ ፣ የትምህርት ዝግጁነት ፣ የእቅድ አዘገጃጀት ፣ የእቅድ አቀራረብና ጥያቄዎች የመመለስ ችሎታ እና ቃለ መጠይቅ) ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ተለይተው ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም ተመርጠዋል።

በውጤቱ መሠረት ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡት ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም በእግር ኳስ ሁለተኛ ዲግሪ ባለቤት ሲሆኑ የካፍ A ላይሰንስ ያላቸውና በተለያዩ ክለቦች የስራ ምልድ ያላቸው እንዲሁም በካፍ ኢንስትራክተርነት የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙ ባለሙያ ናቸው።

\"\"

ፌዴሬሽኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ዶ/ር ጌታቸው ቂናጤ እና አቶ ዮሐንስ ሳሕሌ በቅደም ተከተል በተጠባባቂነት መያዛቸው ተመላክቷል።