ትናንት እና ዛሬ መደረግ የነበረባቸው ጨዋታዎች መቼ ይከናወናሉ ?

በከባድ ዝናብ ምክንያት ያልተከናወኑት አራት ጨዋታዎች መቼ እንደሚደረጉ አጣርተናል።

በድሬደዋ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከየካቲት አራት ጀምሮ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎችን ጨምሮ የአስራ አራተኛ ሳምንት እንዲሁም የአስራ አምስተኛ ሳምንት አራት ጨዋታዎች ባማድረግ መጠናቀቁ ይታወቃል።

\"\"

ሆኖም በትናትናው ዕለት መካሄድ የሚገባው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ በድሬደዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት እንደማይደረግ ተገልጿል። በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት እንዲደረጉ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታዎች የውድድሩ የበላይ አካል ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ እንደማይደረጉ አሳውቋል።

ሶከር ኢትዮጵያም ያልተካሄዱት ጨዋታዎቹ በቀጣይ መቼ የሚከናወኑ ይሆናል በማለት ባደረገችው ማጣራት በዛሬ ዕለት ዝናብ በድሬደዋ ሳይዘንብ ከዋል እና ሜዳው ላይ የቋጠረው ውሃ የሚደርቅ ከሆነ የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ጨዋታዎችን ነገ ለማድረግ ሲታቀድ በተጨማሪም የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታዎች በማግስቱ ማክሰኞ ለማድረግ መታሰቡን አውቀናል።

\"\"

ሆኖም ግን ዝናቡ እንደ ትናትናው ዛሬም መዝነቡን የሚቀጥል ከሆነ ሰኞ እና ማክሰኞ ለማደረግ የታሰቡ ጨዋታዎች በተስተካካይ መርሐግብር ተይዘው ወደ ፊት በሚገለፅ ቀን እንዲደረጉ ሀሳብ አለ።