ከፍተኛ ሊግ | የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ክለብ አዲስ አሠልጣኝ ሾሟል

ከፕሪምየር ሊጉ ከወረደ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ እየተሳተፈ የሚገኘው ክለብ አሠልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን ቀጥሯል።

\"\"

የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ ባደገበት 2010 ላይ ካሳካ በኋላ በሊጉ ውጣውረዶችን አሳልፎ ባለፈው ዓመት ከሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ወደ ታችኛው የሊግ መደብ ወርዶ በአሰልጣኝ የሱፍ ዓሊ እየተመራ በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ ስር ተደልድሎ ደካማ የአንደኛ ዙር ተሳትፎን ያደረገውና በ11 ነጥቦች 11ኛ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀው ጅማ አባጅፋር አሰልጣኝ የሱፍን በማሰናበት በምትኩ ከዚህ ቀደም ያሰለጠኑትን አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን በሁለተኛው ዙር ቡድኑን ለማሻሻል በአሰልጣኝነት ሾሟል።

\"\"

ከዚህ ቀደም ጅማ አባጅፋርን ጨምሮ ዐየር ኃይል ፣ ሰበታ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደጉት አሰልጣኙ ኢትዮጵያ ቡና እና ደቡብ ፓሊስን የማሰልጠን ዕድልንም ያገኙ ሲሆን ኤሌክትሪክን አሳድገው በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ቡድኑን የተወሰኑ ጨዋታዎችን መርተው መለያየታቸው አይዘነጋም።