ከፍተኛ ሊግ | ሀምበሪቾ ዱራሜ ራሱን ለማጠናከር ዝውውሮች ፈፅሟል

የከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ መሪ የሆነው ሀምበሪቾ ዱራሜ ለሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ የአራት ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል።

\"\"

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ በተለይ ያለፉትን ሦስት የውድድር ዘመናትን ጠንካራ ሆነው ከሚታዩ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ሀምበሪቾ ዱራሜ ባለፈው ዓመት አጋማሽ ቡድኑን በተረከቡት አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ እየተመራ በዘንድሮው የከፍተኛ ሊግ የአንደኛውን ዙር ከ12 ጨዋታዎች በሰበሰበው 28 ነጥቦች ምድቡን እየመራ ያጠናቀወ ሲሆን የካቲት 1 ተከፍቶ ለአንድ ወራት ያህል በሚዘልቀው የዝውውር መስኮት አራት ተጫዋቾችን በማስፈረም ለሁለተኛው ዙር ራሱን ማዘጋጀት ጀምሯል።

\"\"

አቃቂ ቃሊቲን ከለቀቀ በኋላ በያዝነው ጥምቅት ወር የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ፋሲል ከነማ ተቀላቅሎ ከቀናቶች በፊት ደግሞ ከክለቡ ጋር የተለያየው አጥቂው ጉልላት ተሾመን ጨምሮ እስራኤል ታደሰን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (መስመር አጥቂ) ፣ ቶሎሳ ንጉሴ ከቡራዩ ከተማ (የመስመር አጥቂ) እንዲሁም ፍቃዱ አሰፋ ከቡራዩ ከተማ (አማካይ) ማስፈረሙ ታውቋል።