አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል

መጋቢት 15 እና 18 ከጊኒ አቻው ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 23 ተጫዋቾችን መርጧል።

ባለንበት ዓመት በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች በምድብ ተደልድለው የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያከናወኑ የሚገኝ ሲሆን ከቀናት በኋላም ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ይከወናሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በሦስት ቀናት ልዩነት መጋቢት 15 እና 18 ከጊኒ አቻው ጋር ሞሮኮ ላይ ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን አሠልጣኝ ውበቱም ለእነዚህ ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች 23 ተጫዋቾችን መምረጣቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ አሰራር በማኅበራዊ ገፆቹ ይፋ አድርጓል።

\"\"

በምርጫው ላይ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ እና አጥቂው ዮሴፍ ታረቀኝ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋና ቡድን ደረጃ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሲቀርብላቸው ከሀገር ውጪ የሚጫወቱት ሽመልስ በቀለ፣ አቡበከር ናስር እና ከረጅም ጊዜ በኋላ የተጠራው ዑመድ ዑኩሪም ተካተዋል።

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገብረሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ሰዒድ ሀብታሙ (አዳማ ከተማ) እና አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን)

ተከላካዮች

ረመዳን የሱፍ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ብርሀኑ በቀለ (ሀዲያ ሆሳዕና)፣ ሱሌይማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሚሊዮን ሰለሞን (አዳማ ከተማ)፣ ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና)፣ አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ) እና ያሬድ ባዬ (ባህር ዳር ከተማ)

\"\"

አማካዮች

ይሁን እንዳሻው (ፋሲል ከነማ)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሽመልስ በቀለ (ኤንፒ)፣ ከነዓን ማርክነህ (መቻል)፣ ታፈሰ ሰለሞን (ፋሲል ከነማ) እና ቢኒያም በላይ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

አጥቂዎች

ዮሴፍ ታረቀኝ (አዳማ ከተማ)፣ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዑመድ ዑኩሪ (አል ሱዋይቅ)፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና) እና አቡበከር ናስር (ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)