በምድብ ሐ ስር ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው ገላን ከተማ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
የ2015 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በሦስት ምድቦች ተከፍሎ የመጀመሪያው ዙር ተጠናቆ የፊታችን መጋቢት 10 ደግሞ በሁለተኛ ዙር የሚቀጥል ይሆናል። የተለያዩ ቡድኖች በዙሩ ራሳቸውን አጠናክሮ ለመቅረብ ዝውውሮችን እየፈፀሙ የሚገኝ ሲሆን ከእነኚህም መካከል ካለፈው ዓመት ስህተቱ በሚገባ ተሻሽሎ በምድብ ሐ ከመሪው ሀምበሪቾ በአራት ነጥቦች ዝቅ ብሎ በ24 ነጥቦች ሁለተኛ ላይ የተቀመጠው የአሰልጣኝ ዳዊት ታደለው ገላን ከተማ አዳዲስ ሦስት ተጫዋቾችን የስብስቡ አካል አድርጓል።
በዚህም ክንዳለም ፍቃዱ አማካይ ከባቱ ከተማ ፣ ኢብራሂም ባዱ አማካይ ከቡራዩ እንዲሁም እንዳለማው ታደሰ አጥቂ ከቡራዩ ከተማ የክለቡ አዲሶቹ ፈራሚዎች መሆናቸው ተረጋግጧል።