ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ከተማ በአዲሱ አሰልጣኙ መመራት ይጀምራል

በከፍተኛ ሊግ ምድብ \’ሀ\’ ግርጌ ላይ የሚገኘው ቡታጅራ ከተማ የሾማቸውን አዲስ አሰልጣኝ የወረቀት ጉዳዮች ጨርሶ ሁለተኛውን ዙር ይጀምራል።

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ስር ተደልድለው ከሚገኙ ክለቦች መካከል አንዱ ነው ቡታጅራ ከተማ በክረምቱ አሰልጣኝ ያለው ተመስገንን ቀጥሮ የአንደኛውን ዙር ውድድር ጉዞ ያደረገ ቢሆንም በምድቡ ሰባት ነጥብን ብቻ ይዞ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጦ ዙሩን ጨርሷል።

\"\"

ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር መገባደጃ ላይ አሰልጣኝ ያለውን ካሰናበተ በኋላ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳን ወደ ኃላፊነት አምጥቷል። ሆኖም የወረቀት ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው አሰልጣኙ ልምምድ እያሰሩ የነበረ ቢሆንም ሜዳ ላይ ቡድኑን መምራት አልጀመሩም ነበር። ከቀናት በኋላ በሚጀምረው የውድድሩ ሁለተኛ ዙር ግን አዲሱ አሰልጣኝ ቡድናቸውን በጨዋታ ቀናትም መምራት እንደሚጀምሩ እርግጥ ሆኗል።

በሀዋሳ ከተማ የታዳጊ እና የዋና ቡድን ረጅም ቆይታን ያደረጉት አሰልጣኝ አዲሴ ደቡብ ፖሊስ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ካፋ ቡናን አሰልጥነው ካለፉ ጥቂት ሥራ አልባ ወራት በኋላ ነው ቡታጅራን የተረከቡት።

\"\"