የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ

በፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ ከነበሩት ክለቦች አንዱ የነበረው ስሑል ሽረ በቅርቡ ወደ ልምምድ ይመለሳል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ከውድድር ርቀው የቆዩት ስሑል ሽረዎች በቅርቡ ወደ ልምምድ ለመመለስ እንቅስቃሴ መጀመራችው ለማወቅ ተችሏል።

\"\"

በከተማው አቅራብያ የሚገኙ ነባር የክለቡ ተጫዋቾች እና የታዳጊ ቡድን ተጫዋቾች ይዞ ልምምድ ለመጀመር በመስራት ላይ የሚገኘው ክለቡ ቀጣይ ሳምንት ልምምድ ለማስጀመር አቅዶ በመስራት ላይ ይገኛል።

በጉዳዩ ዙርያ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ ያደረጉት የክለቡ ስራ አስከያጅ አቶ ተስፋይ ዓለም ሀሳቡ ከተጫዋቾች የመነጨ መሆኑ ጠቅሰው ዋናው ዓላማውም ተጫዋቾቹ አልባሌ ቦታ ላይ እንዳይውሉ ወደ ስፖርቱ ለመመለስ መሆኑን ጠቅሰዋል።

\” ሀሳቡ ከተጫዋቾቹ የመጣ ነው። ምንም እንኳን የክለቡ መዋቅር ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ባይመለስም ባለን ነገር ተጫዋቾቹን ወደ ስፖርቱ ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ ነን። ዋና ዓላማው ግን ተጫዋቾቹን አልባሌ ቦታ ላይ እንዳይውሉ በማሰብ እና ወደ ስፖርት መንፈስ እንዲመለሱ ያለመ ነው\” ብለዋል።

\"\"