የከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ነገ ይጀምራሉ

የ2015 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች በነገው ዕለት በሦስት ከተሞች ይጀመራሉ። የጨዋታ መርሐግብር እና አጫጭር የዝውውር ጉዳዮችን በተከታዩ ዘገባችን አካተናል።

ቦዲቲ ከተማ

የከፍተኛ ሊጉ የምድብ ለ ተካፋይ ክለብ ቦዲቲ ከተማ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል። ክብሩ በለጠ ከ ጎባ ከተማ ፣ ጌታሁን ሺርኮ ከጎባ ከተማ ፣ ዝናቡ ዳመነ ከንባታ ሺንሺቾ ፣ ማሞ አየለ ከሀላባ እና የቀድሞው የሀዋሳ እና ወላይታ ድቻ አማካዩ ነጋሽ ታደሰን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

አርሲ ነገሌ

በአሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመራው የምድብ ሐ ተካፋዩ አርሲ ነገሌ አራት ተጫዋቾችን ለሁለተኛው ዙር በማስፈረም ለውድድር ራሱን አዘጋጅቷል። አሰፋ ኃይለማርያም ከንፋስ ስልክ ፣ አብዱልሰመድ መሐመድ ከጅማ አባጅፋር በ ኢብራሂም ቢያኖ ከየካ እና ሚሻነው መላኩን ከኮልፌ አስፈርሟቸዋል።

\"\"

ስልጤ ወራቤ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ የመጀመሪያውን ዙር ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ያገባደደው የአሰልጣኝ ኑር መሐመዱ ስልጤ ወራቤ የተከላካይ አማካዩ ጥላሁን በቀለ እና የቀድሞው የወልዋሎ ፣ መቻል እና አቃቂ የመስመር አጥቂ የሆነውን ብሩክ ሰሙን አስፈርሟል።

ቡታጅራ ከተማ

ከሰሞኑ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት ቡታጅራ ከተማዎች በምድብ ሀ ተደልድለው በመጀመሪያው ዙር በደካማ ውጤት ግርጌውን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። በነገው ዕለት በአሰላ ለሚጀመረው የምድቡ ጨዋታቸው በትላንትናው ዕለት እየተጓዙ ባለበት ሰዓት የመኪና አደጋን አስተናግደው የነበረ ቢሆንም የከፋ ጉዳት እንዳልገጠማቸው እና በመልካም ጤንነትም ላይ እንደሚገኙ ሶከር ኢትዮጵያ ማወቅ ችላለች።

ጅማ አባ ቡና

በአሰልጣን አስቻለው ኃ/ሚካኤል መሪነት  ቀዘንድሮው በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ስር ተደልድሎ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ በሚደረገው ፉክክር ጠንካራ ተወዳዳሪ መሆን የቻለው ጅማ አባ ቡና በሁለተኛው ዙር ላይ በምድቡ ጠንክሮ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ ሦስት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ክለቡ አሳውቆናል። በዚሁ መሰረት የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር ኩሴ ሞቼራን ከኮንሶ ፣ በንግድ ባንክ ሲጫወት የነበረው የመስመር ተከላካዩ ጥላሁን ጋቶን እንዲሁም ከነቀምት ከተማ አማካይ የነበረውን አስቻለው ዘውዴ ማስፈረሙ ታውቋል።

በነገው ዕለት የሚጀመረው የከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ሳምንት (14ኛ ሳምንት) የጨዋታ መርሀግብር

ምድብ ሀ አሰላ ከተማ

ቤንች ማጂ ቡና ከ ጋሞ ጨንቻ ዕሁድ 3፡00
አዲስ ከተማ ከ ሰንዳፋ በኬ ዕሁድ 5፡00
ንግድ ባንክ ከ አቃቂ ቃሊቲ ዕሁድ 8፡ዐዐ
ሀላባ ከተማ ከ ቡታጅራ ከተማ ዕሁድ 10፡00
ወሎ ኮምቦልቻ ከ ዱራሜ ከተማ ሰኞ 4፡00
ሰበታ ከተማ ከ ወልዲያ ከተማ ሰኞ 8፡ዐዐ
ጅማ አባቡና ከ ባቱ ከተማ ሰኞ 10፡ዐዐ

\"\"

ምድብ ለ ሀዋሳ ከተማ

ሰ/ሸ/ደብረብርሃን ከ ቂርቆስ ክ/ከተማ ዕሁድ 3፡ዐዐ
ጉለሌ ክ/ከተማ ከ ሻሸመኔ ከተማ ዕሁድ 5፡00
ጂንካ ከተማ ከ እንጂባራ ዩኒቨርስቲ ዕሁድ 8፡00
ካፋ ቡና ከ አዲስ አበባ ከተማ ዕሁድ 10፡00
ንብ ክለብ ከ ከንባታ ሸንሺቾ ሰኞ 4፡00
ነቀምት ከተማ ከ ይርጋ ጨፌ ቡና ሰኞ 8፡00
አምቦ ከተማ ከ ቦዲቲ ከተማ ሰኞ 10፡00

ምድብ ሐ ባቱ ከተማ

የካ ክ/ከተማ ከ ስልጤ ወራቤ ዕሁድ 4፡ዐዐ
ዳሞት ከተማ ከ ሀምበርቾ ዕሁድ 8፡00
ሮቤ ከተማ ከ ገላን ከተማ ዕሁድ 10፡ዐዐ
ፌዴራል ፖሊስ ከ ደሴ ከተማ ሰኞ 4፡00
ቡራዩ ከተማ ከ ኮልፌ ክከተማ ሰኞ 8፡00
ጅማ አባጅፋር ከ ሶዶ ከተማ ሰኞ 10፡00
ነገሌ አርሲ አራፊ ቡድን