\”እንደ ዳዋ ሆቴሳ እና አቡበከር ናስር አይነት ወሳኝ ተጫዋቾችም ሳይኖሩ ጥሩ ቡድን ነው ፤ ጥሩ እግር ኳስ ይጫወታል\” ካርሎስ አሎስ ፌረር

የሩዋንዳው አሰልጣኝ ካርሎስ አሎስ ፌረር ቡድናቸው በኢትዮጵያ በአቋም መፈተሻ ጨዋታ የአንድ ለባዶ ሽንፈት ከገጠመው በኋላ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።

ስለ ጨዋታው…

\”የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ቡድን እንደሆነ እናውቃለን። እንደ ዳዋ ሆቴሳ እና አቡበከር ናስር አይነት ወሳኝ ተጫዋቾችም ሳይኖሩ ጥሩ ቡድን ነው ፤ ጥሩ እግር ኳስ ይጫወታል። ጨዋታው ሚዛናዊ ነበር። በእኛ በኩል አጋማሽ ላይ ሁሉም ተጫዋቾች ቀይረናል ፤ ምክንያቱም ለቀጣዩ የቤኒን መደበኛ ጨዋታ ለመዘጋጀት።

\"\"

በዳኛነት ላይ ስላላቸው አስተያየት…

\”ዳኝነቱ በጣም ጥሩ ነበር ፤ በዚህ ዙርያ ምንም ማለት አልፈልግም

በጨዋታ ከኢትዮጵያ የተሻል ነበርን ብለህ ታስባለህ ?

\"\"

\”ዛሬ ከአራት ወሳኝ ተጫዋቾች ውጭ ነው የተጫወትነው ፤ ቀድመው ወደዛ ያቀኑ ተጫዋቾች አሉን። በእርግጥ ኢትዮጵያም ያልተጠቀመችባቸው ተጫዋቾች አሉ። ለእኛ ግን የዛሬው ጨዋታ ልክ እንደ ልምምድ ነበር ፤ በጨዋታው አጋማሽ ሰባት ተጫዋቾች ነው የቀየርኩት። ምክንያቱም ትኩረታችን ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ ሳይሆን ትኩረታችን ለቤኒኑ ጨዋታ ነበር። ኢትዮጵያ ግን መጨረሻ ላይ ለውጦች አድርጋ ጨዋታውን ለማሸነፍ ተጫውታለች ብዬ ነው የማስበው። ግን ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ነበርን።\”